image
image
image
image
image

የኮሪደር ልማቱ ምቹና የተሳለጠ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ያስቻለ መሆኑን ተገለፀ

ግንቦት 16/09/2018, 2018
የኮሪደር ልማቱ ምቹና የተሳለጠ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ያስቻለ መሆኑን ተገለፀ ላፍቶ ግንቦት16/2018፥የኮሪደር ልማቱ ምቹና የተሳለጠ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ያስቻለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገልጿል። በክፍለ ከተማው ከሳርቤት -ጀርመን ጋርመንት- ፉሪ አደባባይ የለማው የኮሪደር ልማት ለትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ምቹ መደላደልን የፈጠረ ከመሆኑ ባሻገር ሰፋፊ መንገዶች፣ ዘመናዊ ተርሚናል ፣ዲጂታል የመንገድ ደህንነት ካሜራዎችን በውስጡ ያከታተ መሆኑ ተመላክቷል። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ ኃላፊ ወ/ሮ ውቢት ዲንቃ፦ ከለውጡ ወዲህ ሪፎርም ከተደረገባቸው ተቋማት አንዱ ትራንስፖርት ዘርፍ መሆኑን ገልጸው የኮሪደር ልማቱ ምቹና የተሳለጠ የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ያስቻለ መሆኑን ገልፀዋል። አገልግሎቱን ለማሳለጥ ከተሰሩ ስራዎች መካከል ምቹ ተርሚናሎች፣ደህንነታቸው የተጠበቁ ካሜራዎች፣ የትራንስፖርት ቁጥጥር ሂደቱን ለመከታተል የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሽ ናቸው ያሉት ኃላፊዋ ሂደቱን ለሚያሳልጡና የቁጥጥር ስራዎችን ለሚሰሩ በርካታ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ያስቻለ መሆኑንም ነግረውናል ። በቄራ ተርሚናል የዲጂታል አሻራ አገልግሎትን ሲሰጥ ያገኘነው ወጣት ቻሌ ፥አሁን ላይ ያለው የትራንስፖርት አገልግሎት ምቹና ዲጂታል ከመሆኑ ባለፈ ከገንዘብ ንኪኪ የፀዳ በመሆኑ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በማስቀረት መንግስት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እንዲያገኝ ያስቻለ መሆኑን ገልጿል። በወረዳ 15 ታክሲ ተርሚናል ተራ አስከባሪ የሆነችው ወጣት ከበቡሽ ደስታ፥ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ የተገነቡ ተርሚናሎች ሰፋፊ መንገዶች ለአገልግሎት አስጣጡ ምቹና ከዚ በፊት የነበሩ ኃላ ቀር አሰራሮችን ያስቀረ ነው ብላለች። የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትም "በጎ አገልጋይ አመስጋኝ ተገልጋይ" በሚል መሪ ሀሳብ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ለሚኖሩ ማንኛውም ጥቆማዎች በ 9417 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ገልጿል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች