image
image
image
image
image

በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ቅ/ፅ/ቤት "ዜሮ ህገ-ወጥ ፤ ዜሮ ቅሬታ"መፍጠር በሚል ባጃጆች ተሽከርካሪዎችን የግንዛቤ ሰጡ፡፡

ታህሳስ 15, 2018
በትራንስፖርቱ ዘርፉ አመስጋኝ ማህበረሰብ ለመፍጠር ቴክኖሎጂን በመጠቀም "ዜሮ ህገ-ወጥ ፤ ዜሮ ቅሬታ"በሚል በዘሬው ቀን የንፋስ ስልክ ቅ/ፅ/ቤት ስራአስከጅ አቶ ሱራፌል ባያብል የባጃጆች ተሽከርካሪዎችን፤ባለሙያዎች፣የክፍለከተማው ከትራፊክ ፖሊስ፣ከደንብ ማስከበር፣ የክፍለከተማ ሰላምና ፀጥታ፤በተገኙበት ተሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል፣ ከተሰጣቸው የስራ መስመር ውጭ እንዳይሆኑ መከላከል የሚያስችል በQR* መለየት እንዲችል ይፋ አድረጓል፡፡ በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ቅ/ፅ/ቤት በ6 ክላስተር የሚገኙ 637 ባጃጆችን የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን ሶስት አገልግሎቶችን በቴክኖሎጅ መስጠት ተጀመረ። እንደ አቶ ሱራፌል ገለጰ ቴክኖሎጂው ህገ-ወጥ ታርጋን መቆጣጠር መለየት የሚያስችል፣ ከማህበራቸው አባላት ውጭ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን መቆጣጠር የሚያስችል፣ ከተሰጣቸው የስራ መስመር ውጭ እንዳይሆኑ መከላከል የሚያስችል በQR* መለየት እንዲችል አገልግሎቱንም በፍጥነትና በጥራት መስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል!

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች