`

የዜጎች የስምምነት ሰነድ |
Citizens Charter

የ2018 በጀት ዓመት በቅ/ጽ/ቤታችን የቁልፍና አብይ ተግባራትን ለማስፈፀም በቂ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን ቀደም ሲል የነበረው የአገልግሎት አሠጣጡ ከሌላ የስራ ሂደት ጋር በአንድ ታጭቆ የነበረበት ሁኔታ በመኖሩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አመቺ ያልነበረ በመሆኑ ሠፊ ችግሮችን እያጋጠሙን ቆይተዋል፡፡ በመሆኑም ይህንን ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ባለስልጣን ፈርሶ በቢሮ ስር ከተዋቀረ በኋላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን በመልሶ የማደራጀት ስራ በመስራት የፈጻሚዉን ተግባር እና ኃላፊነት በሚገባ እንዲያዉቅ ግንዛቤ በመስጠት የውጭ እና የውስጥ አገልግሎቶችን ውጤታማነትና ቀልጣፋነት ለማረጋገጥ የሚያዳግቱ የተለያዩ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ እንዲያስችል ተደርጓል፡፡

በዚህም መሠረት የከተማ ትራንስፖርት አቅም በማሳደግ በስምሪትና በቁጥጥር ሚዛናዊ እንዲሆን ለማድረግና የህዝብ ትራንስፖርት ችግር ለመፍታት አቅም በፈቀደ ሁኔታ ተግባሩ በበቂ የሠው ኃይል በማሟላትና ተጨማሪ የድጋፍ ሠጪ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ በማድረግ ያሉትን መደበኛ ታክሲዎች ጨምሮ አገልግሎቱን የተሻለ ለማድረግ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማሳደግ እንዲሁም የነዳጅ ጭማሪን ተከተሎ የታሪፍ ማሻሻያ ቢደረግም ህብረተሰቡን እያማረረ ያለዉን ከታሪፍ በላይ የማስከፈል፤ መስመር የመቆራረጥ ፤መስመር ያለመሸፈን፤ የታሪፍ ዝርዝር ያለማንጠልጠል ፤ያለታፔላ መንቀሳቀስ የመሳሰሉትን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በጅምር ደረጃ ለውጥ ማምጣት የተቻለ ሲሆን በቀጣይ ዘርፉ ከሚሠጠው አገልግሎት አኳያ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና በተለይም በዘርፉ የሚስተዋሉ የብልይሹ አሰራር አስተሳሰብና ተግባር ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ አገልግሎቱ ፈጣን ቀልጣፋና የህዝቡን ፍላጎት እርካታ ያረጋገጠ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችልና ግልፅነትንና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ለማድረግ ይህ የዜጎች የስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡

የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ

  1. የዜጎች የስምምነት ሰነድ ዋና አላማ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው አገልግሎት በመስጠት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ተግባርና ኃላፊነታችን ለመወጣት በጋራ በመሆን ወደ ስራ የምንገባበት ሰነድ ነው፡፡

የዜጐች የስምምነት ሰነድ አስፈላጊነት

  1. ጽ/ቤቱ በሚሠጣቸው አገልግሎቶች ዙሪያ መረጃ እንዲያገኙ ለማስቻል ግልፅኝነት እና ቅንጅታዊ አሰራር ለመፍጠር ነው፡፡
  2. አገልግሎቶቹና አፈፃፀሞችን ደረጃቸው የጠበቀ መሆናቸውን ለማረጋገጥና ወቅታዊ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ቅ/ጽ/ቤቱ ሥራዎችን ለመገምገምና ለመመዘን የሚያስችላቸው መሣሪያ ስለሆነ ነው፡፡

የን/ስልክ ላፍቶ ትራንስፖርት ቅ/ጽ/ቤት ራዕይ ፤ ተልዕኮ እና እሴቶች

    የን/ስልክ ላፍቶ ትራንስፖርት ቅ/ጽ/ቤት ተግባራት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Mission and Vision ይጫኑ

ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች

  1. ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት፣
  2. የህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትና አገልግሎት ማሻሻል፣
  3. ባለድርሻ አካላትን /የትራንስፖርት ማህበራትን ብቃት ማሳደግ፣
  4. ውጤታማ የሀብት አጠቃቀም ማሻሻል፣
  5. የብልሹ አሰራር አመለካከትና ተግባርን መቀነስ፣
  6. የፈፃሚውንና የአመራሩን አቅም ማሳደግ፡፡

የስትራቴጂካዊ ውጤት

  1. የከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ፍትሃዊና ዘመናዊ በማድረግ አቅርቦትንና ፍላጎት በማጣጣም የህብረተሰብ እርካታን ማረጋገጥ ነው፡፡

የተገልጋዮች አገልግሎት የማግኘት መብት

  1. በተቀመጠ የአገልግሎት አሰጣጥ መሠረት በአግባቡ መጠቀም፣
  2. አካል ጉዳተኞች አረጋዊያንና ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች በቅድሚያና በልዩ ትኩረት የመስተናገድ አገልግሎት ማግኘት፣
  3. ቅሬታና አስተያየት የማቅረብና ላቀረቡት ቅሬታ ወቅታዊና ፍትሃዊ ምላሽ ማግኘት፣
  4. የተቋሙ እቅድና የአፈፃፀም ስርዓት መረጃ የማግኘት፣
  5. ወቅታዊና ተገቢ ምላሽ በማያገኙበት ጊዜ ለሚዲያ፣ ለህዝብ እንባ ጠባቂ፣ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና ሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቅ፣
  6. ደጋፊ ማስረጃዎች ካሉ በአባሪነት ማያያዝ፡፡

የተገልጋዩ ግዴታ

  1. ጽ/ቤቱ አገልግሎቱን ለመስጠት ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልቶ መገኘት፣
  2. በአገልግሎት አሰጣጡ የሚታዩ የጽ/ቤቱና የመንግስት ተልዕኮ የሚያደናቅፍ መሰናክሎች፣የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባራትን የመቃወምና የማጋለጥ ግዴታ አለባቸው፣

የተቋሙ ግዴታ

  1. አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ግብአቶች አሟልቶ መገኘት፣
  2. በተቀመጠው የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት በክብር የማስተናገድ፤
  3. ለተገልጋዮች ፍትሃዊ፤ አድሎ የሌለበት አገልግሎት የመስጠትና በእኩልነት የማገልገል፣
  4. ቅሬታና አስተያየት ለመቀበልና ለመፍታት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት የመዘርጋት፤
  5. ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ፍትሀዊና ፈጣን ምላሽ የመስጠት፤
  6. ለተገልዮች የተቋሙን ዕቅድና የአፈፃፀም ሪፖርት ግልፅ ማድረግ አለበት፤
  7. በዜጎች የስምምነት ሰነድ መሰረት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አስፈላጊ ግብዓቶችን የማሟላትና ተቋማዊ አቅም የመገንባት ግዴታ አለበት፡፡