image
image
image
image
image

‹‹በትራንስፖርት ዘርፍ አመስጋኝ ማህበረስብ እንፈጥራለን!›. በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡

ጥቅምት 16, 2018
በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት የትራንስፖርት ዘርፉን በማዘመን በተሰሩት እና በሚሰሩ ስራዎች የሚያመሰግን ማህበረሰብ እንፈጥራለን በሚል ዕሳቤ ሁሉን አቀፍ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ መክፈቻ ላይ የቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው እንደገለፁት ከተማዋ በፈጣን የልማት ግስጋሴ ውስጥ እንደመገኘቷ መጠን የትራንስፖርት ዘርፉን ተደራሽ፣ምቹ፣ከባቢያዊ ተስማሚነቱ የተረጋገጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በዘርፉ አመስጋኝ ህብረተሰብን ለመፍጠር እንዲያስችል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የገለፁት አቶ ዳኛቸው በመሰረተ-ልማት ዝርጋታዎች፣በተሸከርካሪ ጥራት፣በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት፣በአቅርቦት፣የትራፊክ አደጋን በመቀነስ እና ሌሎች ትኩረት በሚሰጥባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ቢሮው ጠንክሮ እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ በቢሮው የንፋስ ስልክ እና ላፍቶ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሱራፌል ባያብል በበኩላቸው ከተማዋ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ተመራጭ ከማድረግ አኳያ እየተሰሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልፀው ውይይቱ በትራንስፖርቱ መስክ የጎደለውን በማሟላት የታዩትን ጥንካሬዎች በማስቀጠል ውጤታማ ተግባር ለመፈፀም እና የሚያመሰገን ማህበረሰብ ለመፍጠር እንደሚያስችልም አስታውቀዋል፡፡ በውይይቱ ‹‹ትራንስፖርትና ከተሜነት›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በተጋበዙ እንግዳ ጥናታዊ ፅሁፍ የቀረበ ሲሆን ‹‹አዲሷ አዲስ አበባና ትራንስፖርት›› በሚል ሀሳብም ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ እና ከቅርንጫፍ ፅሀፈት ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ከክፍለከተማ አመራሮች፣አባገዳዎች፣አሽከርካሪዎች፣ማህበራት፣የተርሚናል ኢንተርፕራይዞች፣ከተለያዩ አካላት የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተካፋይ ሆነዋል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች