image
image
image
image
image

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፓርት ቅ/ጵ/ቤት ቢሮውን በዘመናዊ መንገድ ሰርቶ አስመርቋል።

ህዳር 21, 2018
በትራንስፓርት ዘርፍ አመስጋኝ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚደረግ ሂደት የስራ ቦታን ምቹ ማድረግ አንዱ ተግባር ነው። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፓርት ቅ/ጵ/ቤት ቢሮውን በዘመናዊ መንገድ ሰርቶ አስመርቋል። ቢሮውን የመረቁት የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢር ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ ባደረጉት ንግግር፤ የትራንስፓርት ዘርፉን ለማዘመን ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፓርት ቅ/ጵ/ቤት ቢሮውን በአዲስ ከመስራትና ለስራ ምቹ እንዲሆን ከማድረጉ ባሻገር ዘመናዊነትን የተላበሰ አሰራር ለመከተል ዌብሳይት በመክፈትና ካሜራዎችን በየቦታው በመትከል የሰራው ስራ ለሁሉም ፅህፈት ቤቶች አርዓያ መሆኑን ገልፀዋል። በተለይም የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፓርት ቅ/ጵ/ቤት "ፅዱ አዲስ ትራንስፓርት" በሚል ያስጠናው ፁሁፍ በከተማ ደረጃ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፓርት ቅ/ጵ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሱራፌል ባያብል በበኩላቸው፤ ዘርፉን ተመስጋኝ ለማድረግ በትብብር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፓርት ቅ/ጵ/ቤት ቢሮ በሁለንተናዊ መልኩ ታድሶ ተመርቋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች