image
image
image
image
image

በቢሮው እና በሸገር ከተማ ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት መካከል ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የህበረተሰቡን እርካታ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

ጥቅምት 27, 2018
በአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ እና በሸገር ከተማ ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት መካከል የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን በማጠናከር ፣ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት እና የተናበበ የትራንስፖርት ስርዓትን በመዘርጋት የህብረተሰቡን እርካታ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገላፀ፡፡ በቢሮ እና በፅህፈት ቤቱ መካከል የ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የጋራ ዕቅድ አፈፃፀምን በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለከተማ በገመገሙበት ወቅት እንደተገለፀው በትራንሰፖርቱ መስክ የሚስተዋሉ ችግሮችን እና የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በጋራ ተቀናጅቶ በመፍታት የተገልጋዩን እርካታ የማረጋገጥ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል፡፡ በውይይቱ በአንደኛው ሩብ ዓመት በቅንጅታዊ ስራ የታዩትን ውጤታማ ተግባራት በተለይም ህገወጥ የትራንስፖርት እንቅስቃሴን በመቆጣጠር፣የምሽት ትራንስፖርትን በማጎልበት፣የብዙሃን ተደራሽነትን በማስፋፋት፣የተቀናጀ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ፣የስምሪትና ቁጥጥር ስርዓትን ወጥነት በመተግበር እና በማጠናከር፣አቅርቦትንና ፍላጎትን በማጣጣም ዙሪያ በመናበብ እና በጋራ ቅንጅታዊ ስራ በመስራት የህብረተሰቡን እንግልት በመቀነሰ የትራንስፖርቱን መስክ እርካታ ማረጋገጥ እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ውይይቱን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራውና የሸገር ከተማ ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ያሲን አህመድ መድረኩን በጋራ የመሩ ሲሆን የቢሮ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችና የሸገር ከተማ ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት የክፍለከተሞቹ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች