image
image
image
image
image

ከጅኦ ስትራቴጂካዊ ኩስመና ወደ ተሻለ ቁመና በሚል መሪ ሃሳብ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ ።

ጥቅምት 1, 2018
በአዲስአበባ ትራንስፖርት ቢሮ ን/ስ/ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት "ከጅኦ ስትራቴጂካዊ ኩስመና ወደ ተሻለ ቁመና" በሚል መሪሃሳብ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሂዷል። የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሱራፌል ባያብል ኢትዮጵያ ያሏትን ተፈጥሯዊ ጸጋዎቿን በመጠቀም ከነበረችበት የኩስመና ጊዜ ተላቃ ወደ ተሻለ ጅኦስትራቴጂካዊ ቁመና የመሸጋገር አገራዊ ብልፅግና ላይ እንደምትገኘና ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር በር ተጠቃሚነት በራሷ ዜጎች የተገለለችበትን እኩይ ሴራ በአለም አቀፍ ህግ የባህር በር ባለቤትነት የምንመልስበት ጥያቄ በማቅረብ በብዙዎቹ የአለም አገራት ተቀባይነት እያገኘች በመሆኑ የባህር በር ጥያቄ ሁሉም ዜጎች ሊደግፉት እንደሚገባ ገልፀዋል። የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ለሁለንተናዊ ብልፅግና እውን መሆን ሁላችንም የሚጠበቅብንን እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች