የባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት
የን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ
- በአገልግሎት ሰጪና በተሳፋሪ መካከል የሚኖረው ግንኙነት ጤናማ እንዲሆን መደገፍ፣
- የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን በማስተጓጎል ችግር የሚፈጥሩ ወይም ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዩች ሲያጋጥሙ ወይም ትክክለኛ መረጃ ሲገኝ ለጥምር ኮሚቴው አስተባባሪ አካል ተገቢ ጥንቃቄ እንዲደረግ ሪፖርት ማድረግና ማገዝ፣
የመካኒሳ ዴፖ ሲቲ ባስ አገልግሎት ድርጅት
- የትራንስፖርት አቅርቦት እጥረትን ለመቅረፍ ለሚጠየቁ ድጋፎች ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- የድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥ ስልት መንደፍና ተግባራዊ ማድረግ፣
- ወደ ክፍለ ከተማዋ የሚገቡ አውቶቡሶች አገልግሎትና ድጋፍ አፈፃፀም /ፐርፎርማንስ/ መረጃ ማቅረብ፣
- የተሽከርካሪ ፍላጎት እና እጥረት ባለበት መስመር ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችን ይመድባል፡፡
የን/ስ/ላ/ ክ/ከተማ ትራፊክ ማነጅመንት ጽ/ቤት
- በትራንስፖርት አገልግሎት ክትትልና ቁጥጥር ስራ ቀጥተኛ ተሣትፎ ማድረግ፣
- የትራፊክ አደጋ መረጃዎችን መያዝ፣ ማደራጀትና ለትራንስፖርት ጽ/ቤት ሪፖርት መስጠት፣
- የተበላሹ፣ የተቀነሱ፣ ያልተሟሉ የመንገድ ላይ ምልክቶች፣ ቀለም ቅቦችና ጥገና የሚያስፈልጋቸውን መንገዶች /ቦታዎችን/ መለየትና እንዲሟሉ ማድረግ፣
- በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ፣የትምህርትና ስልጠና የድጋፍ ስራዎች ላይ መሣተፍ፣
የን/ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
- የትራፊክ ፍሰትን የሚያውኩና የሚገቱ ተግባራትን በመለየት ችግሮችን በመከታተልና በመቆጣጠር፣ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ፣
- ህገ-ወጥ የመንገድ ላይ ንግድ የመከላከል ስራ ይሠራል፣
- በተገቢው ቦታ ያልተሰቀሉ እይታን የሚያውኩ ወይም ፈቃድ ያላገኙ ማስታወቂያዎችና ቢል ቦርዶችን መከታተልና እንዲወገዱ ማድረግ፣
- በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ተሽከርካሪ በማቆም ወይም በየስርቻው /ጋራዦች/ በመደበቅ ወይም ቀን ቀን ተሽከርካሪን ከስምሪት ውጪ አቁመው ምሽት /ሌሊት/ አገልግሎት ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎችን መቆጣጠርና ተገቢውን እርምጃ መውሰድ፡፡
የን/ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት
- ህገ ወጥነትን የመከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማድረግ፣
- የመንገድ ላይ ንግድ ማስቆምና ህጋዊ ንግዶችን ማበረታታት የሚያስችሉ አሰራሮችና ስልቶች ማዘጋጀትና ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ፣
- ወደ ከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ የሚገቡ ባለሀብቶችን የሚያበረታታ የፍቃድ አሰጣጥ ስርዓትን ማጠናከር፣
- ተገቢ ሪፖርት ማደራጀትና ማቅረብ፡፡
የን/ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ስራ እድል ልማት ጽ/ቤት
- ህገ-ወጥ የተራ አስከባሪዎች ወይም በህገ-ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን ህጋዊ ለማድረግ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ፣
- በጽ/ቤቱ የተደራጁ የማህበራትና ኢንተርኘራይዞች በህግና ስርዓት የሚመሩበትን አግባብ ማመቻቸት፣ የአሰራርና የዲሲኘሊን እርምጃ አወሳሰድ መመሪያ ማውጣትና ተግባራዊ ማድረግ፣
- የተርሚናል አስተዳደር አገልግሎት /ደረሰኝ/ የዩኒፎርም ባጅ በማሟላት በተፈቀደው አገልግሎት እንዲካሄድ መደገፍና መከታተል፣ በሚታዩ ጉድለቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ፣
የ3ቱ የታክሲ ባለንብረት ማህበራት
- በቅ/ጽ/ቤቱ የተሠማሩ የኮድ 1 ታክሲ ተሽከርካሪ የሚገቡትንና የማይገቡትን በመለየት መስመራቸውን በማይሸፍኑት ላይ የእርምት እርምጃ በመውሰድ መስመር እንዲገባ ያደርጋል፣
- የትራንስፖርት ፍላጎት መጠንና ስልትን ያገናዘበ ሚዛናዊ የስምሪት ድልድልና ቁጥጥር ማካሄድ፣
- በብልሽት ምክንያት ከስምሪት የሚወጡ ተሽከርካሪዎች /ባለሀብቶች/ ፈጥኖ በማስተካከል ወደ ስምሪት የሚገቡበት የክትትል ስርዓት መዘርጋትና ማስገባት፣
- የታፔላ መስቀያና የታፔላ ምርት ፍላጎትን መለየትና እንዲሟሉ ማድረግ፡፡
የን/ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የተደራጁ ተርሚናል አስተዳደር
- ተሽከርካሪዎች እንደ አመጣጣቸው በተራ ገብተው ተሳፋሪ እንዲጭኑ ማድረግ፣
- የስራ ሰዓት ጠብቀው ስምሪት ላይ የተገኙና ያልተገኙ የመስመር ተሽከርካሪዎች መረጃ ይሰበስባል፣
- ተገልጋዩን ህብረተሰብ እነደአመጣጡ በማሰለፍ ስነምግባር በተላበሰ መልኩ ፍትሃዊ የሆነ የትራንስፖርት እንዲያገኙ ማድረግ፤
የን/ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ምክር ቤት
- ከህብረተሰቡ የሚቀረቡ ቅሬታዎች የይቀበላል
- የተቀበለወን ቅሬታ በፅሁፍ ለቢሮ ግብኣት ይሰጣል
- በየሩብ ዓመቱ ድጋፍ እና ክትትል ያደረጋል ግብረ መልስ ይሰጣል
- በሴክተሩ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራር ካለ መረጃ ይቀበላል
- ቅሬታዎችን እና ብልሹ አሰራር እየታረሙ መሆናቸውን ይከታተላል