መካኒሳ ሲዶ ህንጻ ከ3ኛ-5ኛ ወለል
+251905188881
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
ዓርብ, ህዳር 14, 2016 ዓ.ም
መግቢያ
ስለ እኛ
የቅ/ጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት
የቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
ተቋማዊ አደረጃጀት
የቅ/ጽ/ቤቱ ባለሙያዎች
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
የደንበኞች አገልግሎት
አገልግሎቶች
የተርሚናሎችና መስመሮች መረጃ
የቅሬታ አስተያየት መስጫ
የአገልግሎት እርካታ አስተያየት መስጫ
ለማንኛዉም ጥያቄዎ
የቅ/ጽ/ቤቱን ሮቦት ይጠይቁ
ሚዲያ
ዜና | News
ዶክመንተሪ (ቲቪ)
Video News
መጽሄት | Magazine
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር | Brochure
በራሪ ወረቀት
ማስታወቂያ
ይግቡ
መግቢያ
ስለ እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የዜጎች የስምምነት ሰነድ
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
መጽሄቶች | Magazine
Online TV
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Web APP
ይግቡ
ዜና | Oduu | News
የቂርቆስ እና ልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በንፋስ ስልክ ላፍቶ በመገኘት ልምድ ልውውጥ አደረጉ!
ታህሳስ 27, 2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ "አመሰጋኝ ማህበረሰብ ለመፍጠር" እየተካሄደ ባለው የስራ እንቅስቃሴ በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን ይህንን ተከትሎ የቂርቆስ እና ልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በንፋስ ስልክ ላፍቶ በመገኘት ልምድ ልውውጥ አደረጉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራአስኪያጅ አቶ ሱራፌል ባያብል የቂርቆስ እና ልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለመጡ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ሲያስተላልፉ በተቋሙ ላይ የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በመልካም ተግባር በሰከነ መንገድ መፍታት፣ የተሰጠው አመራር፣ የባለሙያዎች ታታሪነትና ተነሳሽነት እና ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር መኖሩ እንደ እንደ ቢሮ እውቅና የተሰጠው ተግባር መሆኑ ጠቅሶ ወደ ሌሎች ቅርንጫፎች ብወሰድ የተሻለ ተግባር መሆኑ ገልጿል። በልምድ ልውውጡ የቢሮ አደራጃትና ሪፎርም፣ መረጃ አያያዝ፣ ምቹ የስራ አከባቢ/Ergonomics፣ የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ የተሰሩ የቴክኖሎጁ ስራዎችን ሌሎች ለቅርንጫፎች የራሳቸውን ፈጠራ በመጨምር እንደተሞክሮ ማስፋት እንዳለበቸው ተገልጿል። የቂርቆስ እና ልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት እንደገለፁት ያገኙትን ልምድ በቀጣይ የዕቅዳቸው አካል አድርገው እንደሚተገብሩት በመግለፅ ትልቅ ልምድና አቅም ያገኘንበት መድረክ ነው ሲሉ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።
ዜና | Oduu | News
የአዲስአበባ ምክርቤት ትራንስፖርትና ማዘጋጃ ቤታዊ ቋሚ ኮሚቴ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተገኝተው ሱፐርቪዥን አካሄደ።
ታህሳስ 21, 2018
የአዲስአበባ ምክርቤት ትራንስፖርትና ማዘጋጃ ቤታዊ ቋሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ በመገኘት በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ "አመሰጋኝ ማህበረሰብ ለመፍጠር" እየተሰሩ ያሉ ዘረፈ ብዙ ተግባራትን ሱፐርቪዥን አካሂዷል። በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የንፋ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሱራፌል ተቋሙ አመሰጋኝ ማህበረሰብ መፍጠር" በሚል መርህ ሀሳብ ሲያከናውን የነበረውን ተግባራት ለሱፐርዥን ቡድኑ አቅርበዋል።
ዜና | Oduu | News
በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ቅ/ፅ/ቤት "ዜሮ ህገ-ወጥ ፤ ዜሮ ቅሬታ"መፍጠር በሚል ባጃጆች ተሽከርካሪዎችን የግንዛቤ ሰጡ፡፡
ታህሳስ 15, 2018
በትራንስፖርቱ ዘርፉ አመስጋኝ ማህበረሰብ ለመፍጠር ቴክኖሎጂን በመጠቀም "ዜሮ ህገ-ወጥ ፤ ዜሮ ቅሬታ"በሚል በዘሬው ቀን የንፋስ ስልክ ቅ/ፅ/ቤት ስራአስከጅ አቶ ሱራፌል ባያብል የባጃጆች ተሽከርካሪዎችን፤ባለሙያዎች፣የክፍለከተማው ከትራፊክ ፖሊስ፣ከደንብ ማስከበር፣ የክፍለከተማ ሰላምና ፀጥታ፤በተገኙበት ተሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል፣ ከተሰጣቸው የስራ መስመር ውጭ እንዳይሆኑ መከላከል የሚያስችል በQR* መለየት እንዲችል ይፋ አድረጓል፡፡ በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ቅ/ፅ/ቤት በ6 ክላስተር የሚገኙ 637 ባጃጆችን የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን ሶስት አገልግሎቶችን በቴክኖሎጅ መስጠት ተጀመረ። እንደ አቶ ሱራፌል ገለጰ ቴክኖሎጂው ህገ-ወጥ ታርጋን መቆጣጠር መለየት የሚያስችል፣ ከማህበራቸው አባላት ውጭ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን መቆጣጠር የሚያስችል፣ ከተሰጣቸው የስራ መስመር ውጭ እንዳይሆኑ መከላከል የሚያስችል በQR* መለየት እንዲችል አገልግሎቱንም በፍጥነትና በጥራት መስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል!
ዜና | Oduu | News
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ትራንስፖርት ለተቋሙ ባለሙያዎች እና አመራሮች ስልጠና ሰጠ
ታህሳስ 14, 2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ "አመሰጋኝ ማህበረሰብ መፍጠር" እያካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ ሙስናን መከላከል ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል በአዲስ አበባ ትራንስፖርት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሱራፌል ተቋሙ አመሰጋኝ ማህበረሰብ መፍጠር" የመፍጨር ሂደት ውስጥ ለባለሙያ እና አመራር ሙስና እና ሙስናን መከላከል ዙሪያ ስልጠና መሰጠቱ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ገልጿል።
ዜና | Oduu | News
ቅ/ጽ/ቤቱ የትራንስፖርትና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ክላስተር በመቀናጀት የሚሰሩ የ2018 ስራዎች እቅድ የጋራ አድርጓል።
ታህሳስ 1, 2018
በክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ አስተባባሪነት የትራንስፖርትና ማዘጋጃ ቤታዊ ክላስተር የተቋማት ቅንጅት ፊርማ ስነ ስ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የሚመራው የትራንስፖርትና ማዘጋጃ ቤታዊ ክላስተር የተቋማት ቅንጅት ፊርማ ስነ ስርአት አካሂዷል።
ዜና | Oduu | News
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፓርት ቅ/ጵ/ቤት ቢሮውን በዘመናዊ መንገድ ሰርቶ አስመርቋል።
ህዳር 21, 2018
በትራንስፓርት ዘርፍ አመስጋኝ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚደረግ ሂደት የስራ ቦታን ምቹ ማድረግ አንዱ ተግባር ነው። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፓርት ቅ/ጵ/ቤት ቢሮውን በዘመናዊ መንገድ ሰርቶ አስመርቋል። ቢሮውን የመረቁት የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢር ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ ባደረጉት ንግግር፤ የትራንስፓርት ዘርፉን ለማዘመን ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፓርት ቅ/ጵ/ቤት ቢሮውን በአዲስ ከመስራትና ለስራ ምቹ እንዲሆን ከማድረጉ ባሻገር ዘመናዊነትን የተላበሰ አሰራር ለመከተል ዌብሳይት በመክፈትና ካሜራዎችን በየቦታው በመትከል የሰራው ስራ ለሁሉም ፅህፈት ቤቶች አርዓያ መሆኑን ገልፀዋል። በተለይም የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፓርት ቅ/ጵ/ቤት "ፅዱ አዲስ ትራንስፓርት" በሚል ያስጠናው ፁሁፍ በከተማ ደረጃ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፓርት ቅ/ጵ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሱራፌል ባያብል በበኩላቸው፤ ዘርፉን ተመስጋኝ ለማድረግ በትብብር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፓርት ቅ/ጵ/ቤት ቢሮ በሁለንተናዊ መልኩ ታድሶ ተመርቋል።
ዜና | Oduu | News
ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገመገመ፡፡
ጥቅምት 4, 2018
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጆች እና ከማዕከል ዳይሬክተሮች ጋር በመሆን በበጀት ዓመቱ ባለፉት ሶስት ወራት በዕቅድ የያዛቸውን እና ያከናወናቸውን ተግባራት ገምግሟል፡፡ በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም፤ የአገልግሎት አሰጣጥ፤ የመልካም አስተዳደር እና የሀብት አጠቃቀም በማጎልበት ፣የትራንስፖርት መሰረተ ልማትን በማስተዳደር፣የህዝብ እና ጭነት ትራንስፖርት አቅርቦትና አገልግሎት በማሳደግ፣የስትራቴጅክ ጥናት እና የዘርፉን የቴክኖሎጂ አቅም በማጠናከር ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን አስታውቋል፡፡ የሪፎርም ስራ ላይ ትኩረት ተሠጥቶ መሰራታቸው፣ከተቋማትና ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ ስራዎች መጠናከራቸው፣የህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትና አገልግሎት መሻሻላቸው፣የብዙሃን ትራንስፖርት ማጓጓዝ ድርሻ ዕቅድ መሳካታቸው፣የክትትልና ድጋፍ ስርዓታችን መሻሻላቸው፣የኮሚኒኬሽን ስራዎቻችን የዘርፉን ሥራዎችና እንቅስቃሴዎች ያጎላ መሆኑ፤የተለያዩ የክረምት በጎ አድራጎት፣የእንሼቲቭ ሥራዎችንና የ90 ቀን ዕቅድ በአግባቡ ውጤታማ በሆኑ መልኩ ማከናወናቸው በጥንካሬ ተነስተዋል፡፡ በቀጣይነትም የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ስራዎችን በስታንዳርድ መሰረት እንዲከናወኑ ማድረግ፤የምሽት ትራንስፖርት አገልግሎትን ማሳደግ፤የህዝብ ትራንስፖርት የስምሪት ስርዓትን የማሻሻል ስራ ላይ የተለየ ትኩረት ማድረግ፡፡በሌብነትና ክራይ ሰብሳቢነት ላይ ትኩረት በማድረግ እርምጃ የመውሰድ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም በግምገማው ወቅት ተጠቅሷል፡፡
ዜና | Oduu | News
‹‹በሩብ ዓመቱ የታዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ስኬታማነትን ማስቀጠል ይገባል፡፡›› አቶ ያብባል አዲስ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ
ጥቅምት 10, 2018
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የአንደኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን ከአመራርና ባለሙያዎች ጋር በገመገሙበት ወቅት እንደተገለፀው የከተማዋን የትራንስፖርት ሂደት ተደራሽ፣ አስተማማኝ፣ ምቹ፤ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከባቢያዊ ተስማሚነቱ የተረጋገጠ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እተከናወኑ እንደሚገኙ ተገልፅዋል፡፡ የቢሮ ሃላፊ አቶ ያብባል አዲስ እንተናገሩት በሩብ ዓመቱ ከታዩ ስኬታማ ስራዎች መካከል የበጎ አድራጎት እና ኢኒሼቲቭ ስራዎች ፣የአደረጃጀትና አሰራር ተግባራት፣የመመሪያ እና ደንብ ዝግጅቶች፣የፍላጎት እና አቅርቦት የማመጣጠን የተጀመሩ ስራዎች፣የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ተግባራት፣የተካሄዱ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣አሮጌ ተሸከርካሪዎችን በአዲስ ለመተካት የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ስራዎችን በማስቀጠል እና ተግባራትን በላቀ ሁኔታ በመፈፀም በሁለተኛው ሩብ ኣመት ዋንኛ የዕቅድ መተግበሪያ ጊዜ ማድረግ እንደሚገባ አሳታውቀዋል፡፡ የቢሮ የፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዋሲሁን ታረቀኝ በበኩላቸው የታየውን የተሻለ የዝግጅት ምዕራፍ ከግምት በማስገባት በቀጣይነት ከመረጃ አያያዝ ፣ከሪፎርም ስራዎች፣ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ከሰው ሃይል ስምሪት፣ከበጀት አጠቃቀም እና ፋይናንስ፣ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት አንፃር ትኩረት በማድረግ በተሻለ መልኩ መፈፀም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ዜና | Oduu | News
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ትራንስፖርት የአራት ወር አፈፃፀም ገመገመ።
ህዳር 9, 2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ "አመሰጋኝ ማህበረሰብ መፍጠር" በሚል መርህ ሀሳብ ሲያከናውን የነበረውን የአራት ወር አፈፃፀም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ገምግሟል። በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው እና የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሱራፌል ተቋሙ አመሰጋኝ ማህበረሰብ መፍጠር" በሚል መርህ ሀሳብ ሲያከናውን የነበረውን የአራት ወር አፈፃፀም ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
ዜና | Oduu | News
በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፉ አመሰጋኝ ማህበረሰብ የመፍጠር ሂደት የባለሙያ ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ።
ህዳር 8, 2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ አመሰጋኝ ማህበረሰብ የመፍጠር ሂደት ውስጥ የባለሙያዎች ሚና የላቀ እንደሆነ ተገለፀ። በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሱራፌል ባያብል ከባለሙያዎች ጋር አገልግሎት አሰጣጥ፣ ሪፎርም እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ከባለሙያዎች ጋር ውይይት አደረጓል
ዜና | Oduu | News
በቢሮው እና በሸገር ከተማ ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት መካከል ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የህበረተሰቡን እርካታ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
ጥቅምት 27, 2018
በአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ እና በሸገር ከተማ ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት መካከል የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን በማጠናከር ፣ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት እና የተናበበ የትራንስፖርት ስርዓትን በመዘርጋት የህብረተሰቡን እርካታ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገላፀ፡፡ በቢሮ እና በፅህፈት ቤቱ መካከል የ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የጋራ ዕቅድ አፈፃፀምን በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለከተማ በገመገሙበት ወቅት እንደተገለፀው በትራንሰፖርቱ መስክ የሚስተዋሉ ችግሮችን እና የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በጋራ ተቀናጅቶ በመፍታት የተገልጋዩን እርካታ የማረጋገጥ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል፡፡ በውይይቱ በአንደኛው ሩብ ዓመት በቅንጅታዊ ስራ የታዩትን ውጤታማ ተግባራት በተለይም ህገወጥ የትራንስፖርት እንቅስቃሴን በመቆጣጠር፣የምሽት ትራንስፖርትን በማጎልበት፣የብዙሃን ተደራሽነትን በማስፋፋት፣የተቀናጀ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ፣የስምሪትና ቁጥጥር ስርዓትን ወጥነት በመተግበር እና በማጠናከር፣አቅርቦትንና ፍላጎትን በማጣጣም ዙሪያ በመናበብ እና በጋራ ቅንጅታዊ ስራ በመስራት የህብረተሰቡን እንግልት በመቀነሰ የትራንስፖርቱን መስክ እርካታ ማረጋገጥ እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ውይይቱን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራውና የሸገር ከተማ ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ያሲን አህመድ መድረኩን በጋራ የመሩ ሲሆን የቢሮ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችና የሸገር ከተማ ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት የክፍለከተሞቹ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ዜና | Oduu | News
"በትጋት ዜሮ ቅሬታ ፤ ዜሮ ህገወጥ አፈፃፀም ይመዘገባል" - አቶ ሱራፌል ባያብል
ጥቅምት 5, 2018
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰጠው አገልግሎት ላይ ዜሮ ቅሬታና ዜሮ ህገወጥ አፈፃፀም እናስመዘግባለን። በአዲስአበባ ትራንስፖርት ቢሮ ን/ስ/ላፍቶ ቅርንጫፍ በትራንስፖርት ዘርፉ በሚሰጡ አገልግሎቶች በትጋት ዜሮ ቅሬታ ፤ ዜሮ ህገወጥ አፈፃፀም ለማምጣት የሚያስችል የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሱራፌል ባያብል የትራንስፖርት ዘርፉ ላይ የላቀ አገልግሎት በመስጠት ምንም ቅሬታ የማይቀርብበትና ምንም ህገወጥ የሌለበት አፈፃፀም ለማምጣት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
ዜና | Oduu | News
ከጅኦ ስትራቴጂካዊ ኩስመና ወደ ተሻለ ቁመና በሚል መሪ ሃሳብ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ ።
ጥቅምት 1, 2018
በአዲስአበባ ትራንስፖርት ቢሮ ን/ስ/ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት "ከጅኦ ስትራቴጂካዊ ኩስመና ወደ ተሻለ ቁመና" በሚል መሪሃሳብ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሂዷል። የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሱራፌል ባያብል ኢትዮጵያ ያሏትን ተፈጥሯዊ ጸጋዎቿን በመጠቀም ከነበረችበት የኩስመና ጊዜ ተላቃ ወደ ተሻለ ጅኦስትራቴጂካዊ ቁመና የመሸጋገር አገራዊ ብልፅግና ላይ እንደምትገኘና ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር በር ተጠቃሚነት በራሷ ዜጎች የተገለለችበትን እኩይ ሴራ በአለም አቀፍ ህግ የባህር በር ባለቤትነት የምንመልስበት ጥያቄ በማቅረብ በብዙዎቹ የአለም አገራት ተቀባይነት እያገኘች በመሆኑ የባህር በር ጥያቄ ሁሉም ዜጎች ሊደግፉት እንደሚገባ ገልፀዋል። የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች በሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ለሁለንተናዊ ብልፅግና እውን መሆን ሁላችንም የሚጠበቅብንን እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል።
ዜና | Oduu | News
‹‹በትራንስፖርት ዘርፍ አመስጋኝ ማህበረስብ እንፈጥራለን!›. በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡
ጥቅምት 16, 2018
በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት የትራንስፖርት ዘርፉን በማዘመን በተሰሩት እና በሚሰሩ ስራዎች የሚያመሰግን ማህበረሰብ እንፈጥራለን በሚል ዕሳቤ ሁሉን አቀፍ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ መክፈቻ ላይ የቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው እንደገለፁት ከተማዋ በፈጣን የልማት ግስጋሴ ውስጥ እንደመገኘቷ መጠን የትራንስፖርት ዘርፉን ተደራሽ፣ምቹ፣ከባቢያዊ ተስማሚነቱ የተረጋገጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በዘርፉ አመስጋኝ ህብረተሰብን ለመፍጠር እንዲያስችል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የገለፁት አቶ ዳኛቸው በመሰረተ-ልማት ዝርጋታዎች፣በተሸከርካሪ ጥራት፣በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት፣በአቅርቦት፣የትራፊክ አደጋን በመቀነስ እና ሌሎች ትኩረት በሚሰጥባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ቢሮው ጠንክሮ እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ በቢሮው የንፋስ ስልክ እና ላፍቶ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሱራፌል ባያብል በበኩላቸው ከተማዋ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ተመራጭ ከማድረግ አኳያ እየተሰሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልፀው ውይይቱ በትራንስፖርቱ መስክ የጎደለውን በማሟላት የታዩትን ጥንካሬዎች በማስቀጠል ውጤታማ ተግባር ለመፈፀም እና የሚያመሰገን ማህበረሰብ ለመፍጠር እንደሚያስችልም አስታውቀዋል፡፡ በውይይቱ ‹‹ትራንስፖርትና ከተሜነት›› በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በተጋበዙ እንግዳ ጥናታዊ ፅሁፍ የቀረበ ሲሆን ‹‹አዲሷ አዲስ አበባና ትራንስፖርት›› በሚል ሀሳብም ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ እና ከቅርንጫፍ ፅሀፈት ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ከክፍለከተማ አመራሮች፣አባገዳዎች፣አሽከርካሪዎች፣ማህበራት፣የተርሚናል ኢንተርፕራይዞች፣ከተለያዩ አካላት የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተካፋይ ሆነዋል፡፡
መግቢያ
ስለ_እኛ
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፣ ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
አገልግሎቶች
ተቋማዊ አደረጃጀት
ሚዲያ
ዜናዎች | News
ፎቶግራፎች | Photo Gallery
ቪዲዮዎች | Videos
መግለጫዎች | Press Release
መጽሄቶች | Magazine
ጠቃሚ መረጃዎች
ደንብና መመሪያዎች
ብሮሸር
የደንበኞች የእርካታ ዳሰሳ ገጽ
Online TV
Web APP
ያግኙን
laftotransport@gmail.com
+251905188881