የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት ፣ የቅሬታ ወይም የአቤቱታ ይዘትና የአስተያየት መቀበያና መስጫ ስርዓት
የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት
- በስምምነት ላይ በተቀመጠው መሠረት ተገልጋዩ በተሰጠው አገልግሎት ላይ ቅሬታ ካለው በሚከተለው መልኩ ማቅረብ ይችላል፣
- በአገልግሎት አሠጣጥ ላይ ችግር ያጋጠመው ተገልጋይ የቅሬታ አገልግሎት ለፈፃሚ በቃል፣ በፁሁፍ፣ በስልክ ማቅረብ ይችላል፣
- ቅሬታ የቀረበበት አገልግሎት ሰጪ የውስጥ ወይም የውጭ አገልጋይ የቀረበበትን ቅሬታ ጽ/ቤቱ አጣርቶ በፍጥነት ተገቢውን ምላሽ የመስጠት ግዴታ አለበት፣
- በቅሬታ አፈታቱ መፍትሄ ያላገኙ ተገልጋይ ለፈፃሚው የቅርብ ኃላፊ፣ ቅሬታውን እንዲፈታለት ማቅረብ ይችላል፣
- በዚህ ሁኔታ ቅሬታ የቀረበለት የስራ ኃላፊም ቅሬታ አጣርቶ ምላሽ የመስጠት ግዴታ አለበት፣
- በዚህም ያልረካ ተገልጋይ ቅሬታውን ለጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ያቀርባል፡፡ ከሁሉም ሁኔታ አጣርቶ በአጭር ጊዜ ምላሽ የመስጠት ግዴታ አለበት፣
- ከላይ በተዘረዘሩት አካሄዶች በተሰጠው ውሳኔ ችግሩ ካልተፈታለት ወይም የተሰጠው ውሳኔ አግባብ ያለው መስሎ ካልታየው ደረጃውን ጠብቆ ለሚመለከተው የበላይ አካል ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
የቅሬታ ወይም የአቤቱታ ይዘት
ማንኛውም ተገልጋይ ቅሬታውን በፅሁፍ ማቅረብ ከፈለገ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መረጃዎች ማስፈር አለበት፣
- የተገልጋይ ሙሉ ስምና አድራሻ
- ቅሬታ የቀረበበት ዋና ጉዳይ
- መንስኤ የሆነ ድርጊት በአጭሩ ፣ቀንና ቦታ
- ጉዳዩ የተፈፀመበት በተሽከርካሪ ከሆነ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 1 የሆነ የመስመሩ መነሻ እና መድረሻ፣ ኮድ 3 ከሆነ ሠሌዳ የሠጠው ክልል /አአ፣ ኦሮ፣ አማ፣ ደህ.... ወዘተ
- ጉዳዩ የፈፀመው የጽ/ቤቱ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ ስምና የስራ ኃላፊነት
አስተያየት መቀበያና መስጫ ስርዓት
- በተለያዩ ጥቆማዎች ጥያቄ ማቅረብ የሚፈልጉ ግልፅ ባልሆነላቸው ጉዳይ ማብራሪያ የሚሹ ተገልጋዮች እና ባለድርሻ አካላት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የማስተላለፊያ መንገዶች መጠቀም ይቻላል፣
- በተቋሙ የሚገኙ አስተያየት መስጫ ሳጥኖችና መዝገቦች በጽሁፍ
- አገልግሎት የሚሰጥባቸው ጽ/ቤቶች በአካል ተገኝተው በቃል ማቅረብ